Duration 4:38

ኤርቱግሩል | Ertugrul | Ertugrul film Amharic | የሞንጎሎች አስገራሚ ታሪክ ክፍል 1 | dropship,bybit,

1 620 watched
0
22
Published 25 Jun 2021

በዚህ ቪዲዮ የቱርኮች አባት በመባል የሚታወቀውን ኡጉዝ ኻን ማንነት እና አስገራሚ ታእምራቱን እናያለን።ሰብስጅራይብ ያላደረጋችሁ በቀጣይ የምሰራቸው ስራዎች እንዲደርሳችሁ ሰብስክራይብ በማድረግ የደወል ምልክቱን ተጫኑ። ኤርቱግሩል |Ertugrul |Ertugrul film Amharic |የሞንጎሎች አስገራሚ ታሪክ ክፍል 1 #የሞንጎሎች_ታሪክ ከነብዩ ኑህ ( ዐ.ሰ ) እስከ ጄንጊስ ኻን ------------------------------------------------- ( Seid social - ሰኢድ ሶሻል ) ዛሬ የምነግራቸው የአስገራሚዎቹን ህዝቦች የሞንጎሎች ( ሞጉል ) ታሪክ ነው ። እነዚህ አለምን በአንድ እግር ያቆሙት ማንም በታሪክ ያልፈፀመውን ከምስራቁ ጫፍ እስከ ምእራቡ ጫፍ አለምን አንቀጥቅጠው አርበድብደው የገዙት አስፈሪዎቹ ሞንጎሎች ለመሆኑ መነሻቸው ዝርያቸው ከየት ይመዘዛል ? ወደ ሃያልነት ማማውስ እንደት ተቆናጡጡ ? ቱርኮችና ሞንጎሎች ምንና ምን ናቸው ? እነዚህንና መሰል አጃኢብ ታሪኮችን ከ"ቅዱሳን" መፃህፍት እስከ ታሪክ መፅሀፍቶች አገላብጬ ይዤላችሁ ቀርቢያለሁ ። መልካም ንባብ! በመፅሀፍ ቅዱስ በኦሪት ዘፍጥረት ምእራፍ 6 ቁጥር 10 እንደዚህ ይላል " ኖህም ሶስት ልጆችን ካምን ሴምን ያፌትንም ወለደ ። በዚያው ኦሪት ዘፍጥረት ምእራፍ 9 ቁጥር 18 ጀምሮ እንደዚህ ይላል " ከመርከቡ የወጡት የኖህ ልጆች እነዚህ ናቸው ሴም ፥ ካም ፥ ያፌት ካምም የከነአን አባት ነው ።የኖህ ልጆች እነዚህ ሶስቱ ናቸው ከነርሱም ምድር ኹሉ ተሞላች " በማለት ይገልፃል። በመፅሀፍ ቅዱስ ገለፃ መሰረት ኖህ ከማእበሉ መጠናቀቅ በሗላ ገበሬ ሆነ ። እና በዚያ ወቅት ኖህ የወይን ጠጅ ጠጥቶ ሰክሮ ራቁቱን ከቤቱ ወድቆ ነበረ ። ከዚያ ካም ወደ ቤት ሲገባ ኖህ እርቃነ ስጋውን ሆኖ በስካር ራሱን ስቶ ያየዋል ። በዚህ ጊዜ ካም ወንድሞቹን ያፌትንና ሴምን ይጠራና " ኑ የአባታችንን ጉድ ተመልከቱ ሰክሮ ራቁቱን ሆኗል ይላቸዋል ። ሴምና ያፌት ገብተው የአባታቸውን ሀፍረተ ገላ ባዩ ጊዜ ልብስ አልብሰው ይሸፍኑታል ። ከዚያም ኖህ ከስካር መንፈሱ ሲነቃ የተከሰተውን ያያል ። በዚህ ጊዜ ካምን ረገመው ይላል ኦሪት ዘፍጥረት ። " አንተ አገልጋይ የነ ሴም ባሪያ ሁን " ብሎ ረገመው ። በተቃራኒው ሴምንና ያፌትን መረቃቸው ገዥ የበላይ ሁኑ አላቸው ይላል መፅሀፍ ቅዱስ ። በቁርአን አስተምህሮ ግን ነብያቶች ከታላላቅ ወንጀሎች የተጠበቁ በመሆናቸው የመፅሀፍ ቅዱሱ ገለፃ ውድቅ ነው ። ከዚያ በተጨማሪ አላህ የኑህ ( ዐ.ሠ ) ልጆች ሶስት ብቻ እንዳልሆኑ በቁርአን ውስጥ በግልፅ አስቀምጧል። ከማእበሉ ከተረፉት ሶስት ልጆቹ በተጨማሪ አላህ ላይ አምፀው ከተጠፉት ሰዎች ውስጥ የኑህ ልጅ እንደሚገኝበት ቁርአን በግልፅ ያስቀምጣል። " እርሱ ቤተሰቤ ነው " በማለት ኑህ አላህን በተማፀኑት ጊዜ አላህም " እርሱ ከቤተሰብህ አይደለም " ብሎ መለሰላቸው ። እናም ከኑህ ልጆች ሶስቱ ተረፉ ። ካም ሴምና ያፌት! 👉 ካም( ሃም) - የሄደው ወደ አፍሪካ ነው ።የኩሽ የከነአን አባት ነው ። በዚህም የአፍሪካዎች የጥንታዊ ግብፆችና የህንዶች አባት እንድሁም የአይሁዶች አባት ካም ነው ማለት ነው። 👉 ሴም ፦ የሄደው ወደ ኢራን ነው ። የፐርሺያዎች ( የኢራኖች ) የአረቦች እንድሁም የሮሞች ( የአውሮፓዊያን ) አባት ነው ። በነገራችን ላይ የአውሮፓውያን መነሻ ዝርያቸው ፐርሺያ ነው! ክብሯን አንባቢዎቼ የዛሬ ዋነኛ ፅሁፌ የሚያጠነጥነው #የያፌት ልጆች ላይ ነው!!! ያፌት የሄደው ወደ ሩቅ ምስራቅ ነው ። ወደ አሁኖቹ ሩሲያና ካዛኽስታን አጎራባች አካባቢ። ያፌት ስምንት ልጆችን ወለደ ። እነዚህ ስምንት ልጆች የሚከተሉት ናቸው 1 ቱርክ 3 ሩስ 5 ቺን 7 ሰቅለብ 2 ኻዛር 4 ሚንግ 6 ቀመሪ 8 ታሪኽ ቱርክ የቱርኮችና የሞንጎሎች አባት ነው ። ሩስ ደግሞ የሩሲያዎች አባት ነው ። ቺን እና ሚንግ ደግሞ የቻይናዎች አባቶች ናቸው ። ሌሎቹም እንደዚያ በአካባቢው የሰፈሩት የሌሎች ህዝቦች አባቶች ናቸው ። ልብ በሉ ! የእጁጅና መእጁጅ የያፌት ዝርያዎች ናቸው ። ያፌት ቱርክን ተተኪው አድርጎ አለፈ ። ከዚያ ቱርክ ደግሞ ቱቴክን ተክቶ አለፈ ። ቱቴክ ከቱርክ አራት ልጆች ትልቁ ነበር። ከቱርክ አራተኛ ትውልድ ላይ #ታታር እና #ሞጉል የሚባሉ ልጆች መጡና የቱርክን አገዛዝ ለሁለት ከፈሉት ። #ሞጉል_ኻን ቃራ ኻንን ወለደ ። ቃራ ኻን ደግሞ #ኦጉዝ_ኻንን ወለደ ማለት ነው ። አሁን የተገለጠላችሁ ይመስለኛል። ኦጉዝን አስታወሳችሁት አይደል ። የቱርኮች ሁሉ አባት የሆነው ኦጉዝ ኻን ማለት ነው ። እናንተየ ኦጉዝኮ በጣም አስገራሚ ታሪክ ያለው ሰው ነው ። ለመሆኑ ብዙዎች ዙልቀርነይን ኦጉዝ ነው እንደሚሉ ታውቃላችሁ? አሁን ወደ ሌላ የታሪክ ውቅያኖስ አልግባ ። ስለ ኦጉዝ ኻን የቱርኮችን ታሪክ በምፅፍበት ጊዜ አስነብባችሗለሁ። እዚህ ጋር ግን አንድ ነገር ግልፅ ሆኖላችሗል እርሱም ሞንጎሎችና ቱርኮች አንድ ህዝብ እንደነበሩ ! የሞንጎሎችም የቱርኮችም ቅድመ አባት የያፌት ልጅ ቱርክ መሆኑን ። ኢንሻአላህ ስለ ቱርኮች በምፅፍበት ጊዜ ምስሉ የበለጠ ግልፅ ይልላችሗል ። ሞጉል ሞንጎል ሙጋል ተመሳሳይ ተርሞች ናቸው ቱርኮችና ሞንጎሎች በአንድ የቱርክ ስርወመንግስት ስር መተዳደር ጀመሩ ያ ስርወ መንግስት Xiougnu ( ዢዮኙ ) ይሰኛል ። ከቻይና እስከ ሩሲያ አንበርክኮ ያስገበረው ሀያሉ የቱርክ ሞንጎሎች ኢምፓየር ። የዚህ ስርወመንግስት መስራቹ ሞዱን ( Modun ) ይባላል ። ሞዱን ጉደኛ ሰው ነው በጣም ጉደኛ !! ሞዱን አባቱ ከአልጋ ወራሽነት ሊያስወግደው መሆኑን መረጃ በደረሰው ጊዜ ታማኝ ወታደሮቹን ለመፈተንም ሲል አባቱን ግደሉት አላቸው እነርሱም ገደሉት ። በዚህ አላበቃም የወታደሮቹን ታማኝነት ለማረጋገጥ የሚወዷቸውን ፈረሶቻቸውን እንዲገድሉ አዘዛቸው አሁንም ያንን ፈፀሙ። አረመኔው ሞዲን በዚህም አላበቃም ለአርሱ ያላቸውን ታማኝነት ይበልጥ ለማረጋገጥ ሚስቶቻቸውን እንዲገድሉ አዘዛቸው እነርሱም ሚስቶቻቸውን ገድለው አመጡለት ። ከዚያ በሗላ ሞዱንን የሚያስቆመው ሀይል ከቶ አልተገኘም ። ስለ ዢዮንኙ ስርወመንግስት ስለ መሪውም ሞዱን በቱርክ ታሪክ ውስጥ በስፋት እነግራችሖለሁ። እንደማንም ሞንጎሎች በቱርክ ስርወመንግስታት እየተገዙ በርካታ መቶ አመታትን አሳለፉ ። እነ ኻዛርስ ፣ ቃራኻኒድ ኡይጉር ወዘተ በሚባሉ የቱርክ ስርወመንግስታት ስር ሞንጎሎች ጉዟቸውን ቀጠሉ ። እምነታቸው ተመሳሳይ ነበር ። ተንግሪዝም ፣ ሚስቻኢዝም በሗላም ቢድሂዝም የቱርኮችም የሞንጎሎችም የጋራ ሀይማኖቶች ነበሩ ።

Category

Show more

Comments - 4